የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህወሀት የሽብር ቡድን አካባቢውን ወሮ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የዋናው ግቢ ቱሉ አውልያ ካምፓስ አጠቃላይ ግምቱ ከ 12 ሚሊዮን /አስራ ሁለት ሚሊዮን /ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ልዑክ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ‘’የተደረገው ድጋፍ የጠፋውና የወደመው ሀብት በጋራ ተጋግዘን በማሟላት የተቋረጠውን መማር ማስተማር ፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራውን ወደ ነበረበት በመመለስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መሆኑን ተናግርዋል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ‹‹ የተደረገልን ድጋፍ በፍጥነት ወደ ስራ እንድንገባ የሚያግዝና ይበልጥ ለስራ የሚያነሳሳ ስለሆነ ለዩኒቨርሲቲው ከፍ ያለ ምስጋና አለኝ “ሲሉ ተናግረዋል


