“ሀገራዊ የምሁራን ምክክርና ተሳትፎ ለብሄራዊ መግባባትና ለሀገር ግንባታ “በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

Latest News

ታህሳስ 23/2015 ዓ ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት ካውንስል አባላት የተሳተፉበት የመጀመሪያው ዙር ሀገራዊ የምሁራን ምክክር መድረክ ለ2 ቀናት ያክል ከታህሳስ 22-23/2015 ዓ ም ተካሂዷል።በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አብዱ ሁሴን ( ዶ|ር ) እንዳሉትም ውይይቱ ያስፈለገው ምሁራን የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከርና በሀገራችን መፃኢ እድል ላይ የምሁራን ሚና ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ለመምከር መሆኑን ተናግረዋል።የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጌታሁን ጋርደው( ዶ|ር) በበኩላቸው እንደተናገሩት የምሁራን ውይይት ጥቃቅን ልዩነቶችን መራራቂያ ለማድረግ ሳይሆን ሀገራዊ አንድነትንና ልማትን ለማምጣት መሆን አለበት ብለዋል።በእለቱም”የምሁራን ሚና በሀገር ግንባታ” የሚል የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በባለፉት አራት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች፣ ቀጣይ የርብርብ መስክና የምሁራን ሚና የሚሉ ይዘቶች ተብራርተው በተሳፊው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግብአት እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።በቀጣይ ሁለት ቀናትም የዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ መምህራን የሚሳተፉበት ውይይት የሚካሄድ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.