ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የግል ስብዕና ስልጠና ተሰጠ

Latest News

ዩኒቨርሲቲው በአይነቱ ልዩ የሆነ የግል ስብዕና ስልጠና በመዘጋጀት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያክል በሁለቱም ካምፓሶቹ ለሚገኙ መምህራን፣የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች እንድሰጥ አድርጓል፡፡የስልጠናው ይዘትም ህልምን \ Dream / እንደት ማሳካት ይቻላል?የአስተሳሰብ ለውጥ/mind set/፣ የአወንታዊ አመለካከት \attitude\ የማያልቅ ጥቅም፣ድብቁ የአዕምሮ ክፍልን በመጠቀም ለስኬት መብቃት \using subconscious mind for success\፣የአመስጋኝነትና ይቅርባይነት \gratitude and apology\ ትሩፋቶች እንድሁም ሌሎች የግል ስብዕና ላይ ትኩረት ያደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል እንደተናገሩትም ስልጠናው በትውልድ ላይ የአመለካከትና የተግባር ፈጣን ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን በመገንዘባችን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይነት ከዚህ የስልጠና ተቋም ጋር አብሮ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡ስልጠናውን በከፍተኛ ጉጉትና ስሜት ሰልጣኞቹ የተከታተሉት ሲሆን አድሰ እይታና አድስ የአመለካከት ለውጥ እንደፈጠረላቸውም በውይይት ወቅት ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የመካነሰላም ካምፓስ ጀነራል ዳይሬክተር ዶክተር ሺበሺ አለባቸው በበኩላቸው እንደተናገሩት ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ የመጀመሪያው ደረጃ የአመለካከት ለውጥ ላይ መስራት መሆኑን ገልፀው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.