ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) መሰጠት ተጀመረ።

Info Latest News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከዛሬ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀጥታ በበይነ መረብ ከማዕከል ለጤና ተማሪዎች መስጠት ተጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው በት/ርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የግልና የመንግስት ት/ርት ተቋም 213 የጤና ተማሪዎችን ጨምሮ በቀጣይ ቀናት 937 ለመደበኛ እና ለኤክስቴንሽን በጠቅላላ ለ1150 ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል፡:
ዩኒቨርሲቲው ተማሪወችን ለማስፈተን ያደረገው ዝግጅት መልካም መሆኑን የገለፁት ለጤና ተማሪዎች የፈተናው አስተባባሪ ረዳት
ኘሮፌሰር ንጉሴ ቸሬ የፈተናው ሒደትም ፍፁም ሰላማዊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.