ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለሚያስመርቃቸቸው መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ከምረቃ በኋላ ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ መሆን የሚያስችል ክህሎትና ዕውቀት ከኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ ልማት ማህበር ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት በዘርፉ እውቀት ባላቸው ምሁራን ከሃምሌ 16-17/2013 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የውጤታማነት አሰራር ስርዓት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ጋትራይ ቱት እንዳስታወቁት የስልጠናው አስፈላጊነት ተማሪዎች ተመረቀው ሲውጡ ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ መሆን የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸው ስልጠናው ትኩርት ያደረገበት ርዕሰ ጉዳይ፡- ለስራ ፈጠራ ራስን ማዘጋጀት ፤የስራ ፈጠራ ክህሎትን ማሳደግ ፤በአካባቢ የሚገኙ ጸጋዎችን እንደት ወደ ሀብት መቀየር የሚያስችል አቅም መፍጠርና በዕ ቅድ መመራት የሚሉ ወሳኝ ጉዳዎች ላይ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡የስልጠናው ተሳታፊ ተማሪዎች በበኩላቸው ስልጠናው በቀጣይ የግል የዕለት ከዕለት ህይዎታቸው የራስን አውቀት ና ክህሎት በመጠቀም በአካበቢ የሚገኙ ጸጋዎችን እንደት ወደ ሀብት መቀየር እንደሚችሉ ዕውቀት ፣ክህሎትና በራስ የመተማመን ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል ፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.