‹‹ለፍቅርና ለአንድነት›› በሚል መሪ ሀሳብ የስነ ጽሁፍና ኪነ ጥበብ ምሽት ተካሄደ ፡፡

Amharic language and Literature Info Latest News

( ታህሳስ 15/2015 ዓም የኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት)


በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውሊያ ዋናው ግቢ ‹‹ለፍቅርና ለአንድነት›› በሚል መሪ ሀሳብ የስነ ጽሁፍና ኪነ ጥበብ ምሽት በተማሪዎች አዘጋጅነት ታህሳስ 15/2015 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡
በስነ ጽሁፍ ልዩ ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸው መምህራን ና ተማሪዎች ጥበባቸውን ያሳዩበት እንድሁም በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ከተማሪዎች የቀረበ ልዩ አድናቆት ያተረፉ ሙዚቃ፣ውዝዋዜ እና ስፖርታዊ ትርኢት የታየበት ዝግጀት ተካሂዷል ፡፡
በፕሮግራሙ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር አጥቁየ ቸኮል እንዳሉት የስነ ጽሁፍ ና ኪነ ጥበብ ምሽት በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረ መሆኑን ተናግረው በቀጣይ ተማሪዎች፣ መምህራን ና ሌሎችም የግቢው ማህበረሰብ የሚሳተፉበት ጥበብን ለፍቅርና ለአንድነት በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ፕሮግራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ፡፡
ተማሪዎችም በበኩላቸው እምቅ የሆነ የስነ ጽሁፍና ኪነ ጥበብ ችሎታ ያላቸው እድሉን አግኝተው ችሎታቸውን የሚያሳዩበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ጥሩ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም ተጠናክሮ እንድቀጥል ጠይቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.