ለ ደቡብ ወሎ ዞን ከ/ፍ/ቤት ማኔጅመንት አባላትና ና ለወረዳ ሰብሳቢ ዳኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው

Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋር በመተባበር የዞኑ ከ/ፍ/ቤት ማኔጅመንት አባላት፤ የወረዳ ፍ/ቤት ሰብሳቢ ዳኞች የተሳተፋበት ‹‹ በአመራር ጥበብ፣ በጉዳዮች አያያዝ ና አፈታት›› ዙሪያ ከማዚያ 2-4/8/2013 ለ3 ተካታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡የዩኒቨርስቲው የጥናትና ምርምር ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕረዜዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ‹‹ለላቀ የዳኝነት ስርዓት የዳኞቻችንን አቅም እና ጉልበት ፤ ለቀልጣፋ ፍርድ አሰጣጥ ሳይንሳዊ የአሰራር ጥበብን እንሰንቅ ››በሚል አስተሳሰብ የዞናችንን ማህበረሰብ ፍትህ እንዳይጓደል መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የድረሻውን ለመወጣት የታሰበ ስልጠና እንደሆነ ለሰልጣኞች አስገንዝበዋል፡፡የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ጀንበሩ ካሳ በበኩላቸው ‹‹ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በአጭር ጊዜ ተፈጥሮ በዞናችን እየተካሄደ ያለውን የዳኝነት ስርዓት ለማሳለጥ ከተማርነው ትምህርት በተጨማሪ በማሰልጠን ፍትህ እንድሰፍን የተሻለ የፍትህ ስርዓት እንድኖር ስላደረገው ጉልህ ተግባር አመስግነው አጋርነታችንን የበለጠ በማጠንከር አዳድስ የአስራር ጥበቦችን ለማገኘት በቀጣይም በትብብር እንደሚሰራ ለሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.