መቅደላ አምባ ዩኒቨረሲቲ ለግቢው የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከአቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በሁለቱም ግቢ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ሩህሩህ (አዛኝ ) ተገልጋይ አክባሪና ተገቢውን አግልግሎት መስጠትየሚችል ባለሙያ መፍጠር ፤ የተላላፊ በሽታችን መከላከል መቆጣጠር ና ህክምና መስጠት ላይ ያተከረ ስልጠና ከማዚያ 15 /82013 ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት እየተሰጠ ይገኛል ፡፡የመቅዳለ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰው አገኝ አስራት በስልጣነው የመክፈቻ ንግራቸው እንዳሳሰቡት ፡ ‹‹ይህ ስልጠና አቀስታ ጠቅላላ ሆስፒታል የሆነበት ዋና አላማ ከስልጠናው ጋር ተያያዥነት ያላቸው በልምምድ ና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ለመስጠትም ጭምር እንደሆነ ለሰልጣኞች አስረድተዋል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ቡድን መሪ አቶ የማነ ብርሀን ጎሹ በበኩላቸው ስልጠናው ለስራችን መቃናት ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ስልጠናውን እንድከታተሉ አሳስበው በቀጣይም በዙር እንደሚሰጥም አክለው ገልጸዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.