መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነሰላም ግቢ ለሚገኙ የግቢው ተማሪዎች በሀገር ግንባታ የወጣትነት ሚና ላይ ወይይት አደረጉ፡፡

Latest News Research news

በመካነ ሰላም ግቢ ለሚገኙ የግቢው ተማሪዎች በሀገር ግንባታ የወጣትነት ሚና ፣ምርጫና ማህበራዊ መገኛኛ ብዙሃን ፤ ምርጫ፣ ለህቃን፣የዝምተኛው ብዙሃን ሚና በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት መምህራን አማካኝት ውይይት ተደርጓል ፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ግቢ ጀኔራል ዳይሬክተር ዶክተር ሽበሽ አለባቸው ወይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት ‹‹ምክንያታዊ ትውልድ በመሆን ለሀገር ግንባታ የድርሻችንን መወጣት የምንችለው በማይነቃነቅ መሰረት ላይ የተቀመጠ ሀገራዊ አስተሳሰብ መያዝ ስንችል ነው›› ሲሉ ለግቢው ተማሪዎች ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስና አለማቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ና የእለቱ አወያይ መምህር እያሱ ዘለቀ እንደገለጹት ሰነዱ በሀገር ደረጃ የሚሰጥ ሀገራዊ ስልጠና በሆኑ በሁለቱም ግቢያችን የሚገኙ መምህራንና የአሰ/ሰራተኞች በውይይቱ እንደሚሳተፉ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዝግጅት ክፍል አሰታውቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.