መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ግቢ ለሚገኙ አስተዳደር ሰራተኞች የጊዜ አስተዳደር ስርዓት ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው መማር ማስተማር ፤ችግር ፈች ጥናትና ምርምርእና የላቀ የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮውን ለመወጣት የሰው ሀብት ልማቱን በአመለካከት፣ ፣በክህሎት ና በዕውቀት በማበልጸግ የተሻለ ፈጻሚ መፍጠር ቀዳሚ ተግባር በማድረግ የመካነ ሰላም ግቢ የስተዳደር ሰራተኞችን ከግንቦት 24- 27 /9/2013 ዓ.ም በሁለት ዙር የጊዜ አጠቃቀም ስርዓትና የጊዜ አስተዳደር ስርዓት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡የመካነሰላም ግቢ ጀኔራል ዳይሬክተር ዶክተር ሽበሽ አለባቸው ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ‹‹በሰው ልጆች መካከል ልዩነት የሚፈጠረው የጊዜ አጠቃቀም ልዩነታችን ነው፡፡ ጊዜ አለኝ በሚል ሳንፈጽማችው የቀሩ ጉዳዮች ተደራርበው በወቅቱ የምንፈጽመውን ተግባር እንዳናከናውን እንቅፋት ይሆናሉ ፡፡ በሌላው ጎን ደግሞ ተግባራትን በጊዜያታቸው ከተፈጸሙ ሌላ አድስ ነገር ለመስራት አንቸገርም ፡፡ስለሆነም ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም እውቀት ከሁሉም በላይ በላጭ ነው ሲሉ ›› ለሰልጣኙ ያላቸውን ልምድና ምክረ ሀሳብ ለግሰዋል ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ቡድን መሪ አቶ የማነ ብርሃን ጎሹ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ለሰው ሀብት ልማት ቅድሚያ በመስጠት የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እንድንሰጥ በፈጠረልን እድል መሰረት የፈጻሚውን አቅም ለማጎልበት ስልጠናዎችን እየሰጠን እንገኛለን ሲሉ ገልጸው እስካሁን በሰጠናቸው ስልጠናዎች በሰራተውኛው ዘንድ የታየው መሻሻል ጥሩ ነው ነገር ግን ለስልጠናው ትኩረት ስጥቶ መከታተል ብቻ ሳይሆን በተግባረ ተፈጽሞ ሲታይ ያገኛችሁት እውቀት ጥቅም ላይ መዋሉን የበለጠ የምናረጋግጠው በዚህ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.