መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ስራውን ጀመረ!!

Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተለይም በአማራና በአፋር ክልሎች በተፈጠረው የህወሀት ወረራና ዘረፋ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑ ላለፉት አምስት ወራት ከመደበኛ ስራው ውጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡ይሁን እንጂ ዩኒቨርሲቲው ወራሪውና ዘራፊው ቡድን ከቦታው ላይ ከተወገደበት ሰዓት ጀምሮ ምንም አይነት ጊዜ ሳያጠፋ የ60 ቀናት መልሶ መቋቋሚያ እቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር በመግበቱ መደበኛ ስራውን ለመጀመር የሚያስችለው ቁመና ላይ ደርሷል፡፡በዚህም መሰረት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ፣ ማኔጅመንት፣ መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም ድጋፍ የሚያደርጉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የየድርሻቸውን በውቅቱ በመፈፀማቸው ለተማሪዎቹ ጥሪ በማድረግ ከየካቲት 2-3/2014 ዓ.ም ድረስ ተቀብሏል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በመምህራን፣ በአስተዳደር ሰራተኞችና በተማሪዎች ላይ የተፈጠረውን የስነ-ልቦና ስብራት የሚጠግኑ የአዕምሮና የስነ-ልቦና ውቅር ለውጥ ስልጠናዎችን በሁለቱም ግቢዎች በማደራጀት ከ4-5/06/2014 ድረስ በቱሉ አውሊያ ዋናው ግቢ እየሰጠ ሲሆን በመካነ ሰላም ግቢ ደግሞ ከ7-8/06/2014 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ ስልጠና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው ሙያተኞች የሚሰጥ ሲሆን በመምህራን፣ሰራተኞችና ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነትንና ፍላጎትን እንደገና በመቀስቀስ በተሟላ ዝግጁነት መደበኛ ስራቸውን በውጤታማነት ለመፈፀም እንደሚያስችልም የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰዋገኝ አስራት በስልጠና መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ገልፀዋል፡፡የካቲት 4/2014ዓ.ም ቱሉ አውሊያኢትዮጵያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.