መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የጸረ- ሙስናን ቀንን አከበረ።

Info Latest News

ህዳር 23/2015 ዓ ም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በስነ ምግባር የታነፀ አመራር፣ ሰራተኛና ተማሪ ብሎም ከሙስና የፀዳች ሀገር ለመፍጠር በአለም ለ19ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ18 ጊዜ የሚከበረውን የፀረ -ሙስና ቀንን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ፤ የተማሪ ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሺማግሌዎች ፣ከደቡብ ወሎ ዞንና በደቡብ ወሎ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ወረዳ አመራሮች እንድሁም የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች እለቱን አክብሯል።በዚህ አለም አቀፍ የፀረ- ሙስና ቀን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቅደላ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ሹመት አሰፋ (ዶ/ር) እንደተናገሩት አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ከማክበር ባለፈ የሙስናን አስከፊ ገፅታ በመረዳትና የግንዛቤ ስራ በመስራት ከችግሩ ለመውጣት ሁሉም በጋራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በእለቱም በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ መሀመድ ፈንታው እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ተስፋየ የውይይት መነሻ ፅሁም ያቀረቡ ሲሆን በሙስና ላይ ትኩረት ያደረጉ ልዩ ልዩ የስነፅሁፍ ስራዎችም ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡በቀረቡ ሰነዶችም ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ በቀጣይ የፀረ ሙስና ትግል አቅጠጫ ላይ ማጠቃለያ ቀርቦ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦ website- https://mkau.edu.et/ fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University twitter- https://twitter.com/mekdela_amba LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.