መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን የህዝብ ቅሬታ ሰሚ መምሪያ ጋር በመተባበር ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ ፡፡

Research news

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን የህዝብ ቅሬታ ሰሚ መምሪያ ጋር በመተባበር ለመምሪያው የማኔጅመንቱ አባላትና ባለሙያዎች ፣ለወረዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች ‹‹ በማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥና ተጠያቂነት ፣የአቤቱታና ቅሬታ ምርመራ አወሳስን›› በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ከአ/ብ/ክ/መ/ህ ቅሬታ/ሰ/ቢሮ በዘርፋ ሙያ ባላቸው አሰልጣኞች ከሚያዝያ 1-3 /2013 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት የቆየ ስልጠና ተስጥቷል ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ ስልጠናዉን ባስጀመሩበት ወቅት ‹‹መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ‹‹ አዉቀን እናሳዉቅ ፣ተገንዝበን እናስገንዝብ›› በሚል አስተሳሰብ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታን መፍታት የሚችል ሙያተኛ ለመፍጠር እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡የአ/ብ/ክ/መ/ህ /ቅሬታ/ሰ/ቢሮ ተወካይ ወ/ሮ አበበች ዳርጌ በበኩላቸዉ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ያደረገዉ አስተዋፅኦ እጅግ በጣም የሚደነቅ ተግባር እንደሆነ ገልጸዉ በዞኑ ስር ያሉ ወረዳዎች ቅር የተሰኘን ግለሰብ ፈጣን የሆነ ምላሽ በመስጠት ከእንግልትና ዉጣ ዉረድ ለማስቀረት አቅም የሚፈጥር ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.