መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ዝርያ የወተት ላሞችን እና የተዳቀሉ የበግ ዝርያዎችን በማላመድ አዋጭ የሆነ ስራ እየሰራ ነው፡፡

Latest News Research news

ጥቅምት/2015 የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት በዋናው ግቢ ቱሉ አውሊያ ሆለስቲክ ፍሪዥያን የተባሉ የውጭ ዝርያ የወተት ላሞችን እና የወሎ* አዋሲ የተዳቀሉ የበግ ዝርያዎችን በማላመድ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው ፡፡የወተት ላሞቹ በቀን ከ120 ሊትር በላይ ወተት ገቢ የሚያስገኙ ሲሆን ከዚህ ጎንለጎን ዝርያዎቹ ለአካባቢው ማህበረሰብ አዋጭ ዝርያዎችን በመምረጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማርባት እንድቻል ለማስተማሪያነት በመጠቀም ውጤታማ ስራ ለመስራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጻል ፡፡የወሎ አዋሲ የበግ ዝርያዎቹም በአጭር ጊዜ አዋጭ የሆነ ገቢ የማስገኘት እድል የሚፈጥሩ መሆኑ በተግባር የታየ ስለሆነ በቀጣይ በስፋት እንደሚሰራ የቢዝነስና ልማት ዳይሬክተሩ አቶ ታደለ ሙሴ ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.