ዪኒቨርሲቲው የላቀ የቴክኖሎጅ ሽግግር ለማድረግ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመካኒካል ኢንጅነሪን ፈጠራ ስራ የተስራ አድስ የመውቂያና ማጨጃ ማሽን ወደ ዩኒቨርሲቲው በማስገባት ቴክደኖሎጅው ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥቅም ላይ እንድውል በደቡብ ወሎ ዞን ስር ከሚገኙ የሙያና ቴክኒክ ተቋማት የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎችና የፈጠራ ባለቤቶች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት የአጠቃቀም ስልጠናው ተሰጥቷል ፡፡ የፈጠራ ባለቤቶቹ አቶ አበበው ሽመልስ እና አቶ አማር አድስ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት ማሽኑ ከጤፍ ውጭ በሰዓት ግማሽ ሄክታር የሚያጭድና ከ15-40 ኩንታል በስዓት የመውቃት አቅም እንደሚችል ውገልጸዋል ፡፡ማሽኑ የግብርናውን ዘርፍ ከማዘመን ባሻገር የእናቶችና ህጻናት እንግልትን እንደሚቀንስ ገልጸዋል፡፡የስልጠናው ተሳታፍዎቹ ለፈጠራ ባለቤቶቹ ለፈጠራ ስራቸው አድናቆታቸውን ለግሰዋል፡፡
ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!


