ግምገማውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አራት አመታት በ22 የትምህርት ክፍሎች በመጀመሪያ ድግሪ ሲያስተምር የቆየ መሆኑን አስታውሰው በተጨማሪም ፕሮግሞቹን ለማሳደግ 6 የመጀመሪያ ግድሪና 4 የሁለተኛ ድግሪ ለመክፈት አቅዶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡አሁንም የዚህ አካል የሆነው በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት የትምህርት ክፍሎች ማለትም MSC. In Development Economics, MA in Teaching English as a foreign Language/TEFL/, MSC in Animal Production የማስተርስ ፕሮግራም ለመክፈት ጥራቱን የጠበቀ ካሪኩለም እንድዘጋጅ በውጭ ገምጋሚወች ማስገምገሙ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
እነዚህ ፕሮግራሞች በትምህርት ክፍሎች፣በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲው ሴኔት በየደረጃው ውይይት ተደርጎባቸው የትምህርት ተደራሽነትንና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሚኖረው ፋይዳ አኳያ እንድከፈቱ ውሳኔ የተደረሰባቸው ሲሆኑ ትምህርቱንም ለማስጀመር በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የተማሪ ጥሪ በማድረግ በቱሉ አውልያ ካምፓስ MSC. in Animal Production እና በመካነሰላም ካምፓስ MSC. In Developmente Economics and MA. in Teaching English as a foreign Language/TEFL/ በቅርቡ ማስተማር እንደሚጀምርም አክለው ገልፀዋል፡፡
መስከረም 27/2014 ዓም



