ማርች 8-ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓልን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡

Latest News

በየዓመቱ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት መጋቢት 8 እና በኢትዮጵያዊያን የዘመን ቀመር ደግሞ የካቲት 29 “የዓለም ሴቶች ቀን” ይከበራል፤ ቀኑ በተደጋጋሚ “ማርች 8” እየተባለ ሲጠራም እንሰማለን፡፡ የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የሴቶችን መብት የሚያከብር ማኅበረሰብ እንገንባ!” በሚል መሪ መልዕክት በዓለም ለ110ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲም ሴት መምህራንና የአስተዳር ሴት ሰራተኞች በተገኙበት የካቲት 29/2013 ዓ.ም በፓናል ውይይት ተከብሮ ውሏል፡፡ የፓናል ውይይቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ጌታሁን እንደተናገሩት ሴቶች 50% በላይ የማህበረሰባችንን ክፍል የሚይዙ በመሆኑ እነሱን በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅም ብቁ ማድረግ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት የማይተካ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በፓናል ውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ማህበር እቅድ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ሪፖርቱን ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት መምህርት ስዓዳ እንድሪስ እንደተናገሩት ሴቶች በተለያየ አደረጃጀቶች ውሰጥ መሳተፋችን በሁሉም ዘርፍ አቅማችንን በማሳደግ መሆን ያለብበንን ለመሆን፣ጥቃቶችን ለመከላከል እና መብታችንን ለማስከበር ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አበበ ጸጋ በቀረበው የፓናል ፅሁፍና አድስ ማህበር መመስረት አስፈላነት ላይ ውይይት እንድካሄድ አድርገው ሴት የአስተዳደር ሰራተኞች ማህበር ተመስርቶ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት፡-website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን! የካቲት 30/2013

Leave a Reply

Your email address will not be published.