በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የምሁራን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

Info

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች የተሳተፉበት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሚመክር ውይይት ተካሂዷል፡፡በውይይቱም በርካታ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የተዳሰሱበት ሲሆን በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የምሁራን የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገልፀዋል፡፡የውይይት መድረኩን ሲያተባብሩ የነበሩት በመካነሰላም ካምፓስ መምህር የሆኑት አቶ እያሱ ዘለቀ እንዳሉትም ምንም አይነት ፈተና ቢኖር በሀገር ተስፋ ስለማይቆረጥ ምክኒያታዊ የሆነ ትውልድ በመገንባት የህግ የበላይነት እንድሰፍን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ሌላው የውይይቱ መሪና በመካነሰላም ካምፓስ መምህር የሆኑት አቶ ሰለሞን እሽቱ በበኩላቸው እንደገለፁት ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት በተስፋና በስጋት መንታ መንገድ ላይ የምትገኝ በመሆኗ ይህን ወቅት በጥበብ መሻገር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡በውይይቱ ላይ የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ግብአት ይሆኑ ዘንድ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚላክ ተገልፀዋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.