በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱም ካምፓሶች የስነምግባርና ፀረመስና ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

በአማራ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አማካኝነት  ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  በሁለቱም ካምፓስ ለሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ  አመራሮችና ወሳኝ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ  ባለሙያዎች  በስነምግባርና ፀረሙስና ዙሩያ ላይ  ለ142ያክል ተሳታፊዎች  ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ የስነምግባር ማንነት፣የስነምግባር አስፈላጊነት፣የስነምግባር ምንጮች፣የስነምግባር ችግር የሚያስከትለው ጉዳት፣የሙስና ትርጉም፣የሙስና መገለጫዎች፣የሙስና ጉዳትና መከላከያ ስልቶቹ የሚሉ አርዕስቶች ተነስተው ተብራርተዋል፡፡

በአማራ ክልል  የደሴ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አብዱ መሀመድ እንደገለፁት የሙስናን ጉዳት በመረዳትና  በመጠየፍ ስብዕናችንን በሰነምግባር በማነፅ መንቀሳቀስ እንደግለሰብ ብሎም እንደ ሀገር አስፈላጊና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሰነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ ፈንታው በበኩላቸው እንደገለፁት  ግብአት በማሟላት ና ቅደመ ዝግጅት ከማድረግ ጀምሮ  ስለጠናውእንድሰጥ  በማመቻቸት በተደረገው ጥረት ሳቢና ማራኪ በሆነ መልኩ ትምህርቱ እድተላለፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት ይህ አይነቱ ስልጠና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገኙ አካላት መሰጠቱ ሀገራችን አሁን ካለችበት የሙስና ችግርና የወጣቶች የስነምግባር ጉድለትን ለማረም ወሳኝ በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶበት ተመሳሳይ ስልጠናዎች በስፋት መሰጠት እንዳለበት  ተናግረዋል፡፡ i-font-d3��w

Leave a Reply

Your email address will not be published.