በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱም ካምፓሶች የሚገኙ ሰራተኞች በኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ 62 ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቭረሲቲ  ምንም እንኳንተመርቆ  ስራ ከጀመረ  ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ካሉት ትልልቅ  ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ  የማህበረሰብ አገልግሎት በመሆኑ የአካባቢውን ህብረተሰብ ችግር እየለየ በየጊዜው የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህንንም  ተልዕኮ በመደገፍ የዩኒቨርስቲው መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ካላቸው ላይ በማካፈል በቱሉአውሊያ ካመፓስ  10500/አስር ሺ አምስት መቶ/ ብር እና በመካነ ሰላም  8450 /ስምንት ሺ  አራት መቶ ሃምሳ / ብር  በድምሩ  18950 /አስራ  ስምንት  ሺ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ / ብር በማዋጣት   ለ62  ተማሪዎች የዩኒፎርም ድጋፍ አድርገዋል፡፡

‹ይህ ዪኒቨርቲ  የተቋቋመው አካባቢውን ለመለወጥ ሩቅ በማሰብ ነው› ያሉት የጥናትና  ምርምር እና  ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘንዳንቱ ዶ/ር ወንድዬ አድማሱ በቀጣይም  በኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የመደገፍ ፣ ችግሮችን   በጥናትና ምርምር የመለየት እንድሁም የአካባቢውን ተፈጥሯዊ ሁኔታ የማሻሻልና  የመለወጥ ስራ ይከናወናል ብለዋል፡፡ 

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የተማሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው ዪኒቨርስቲው ከጅማሮው ለማህበረሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ  እና አካባቢውን የመለወጥ እንቅስቃሴ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በቱሉአውሊያ  ከተማ የሃይማኖት አባት የሆኑት  ሸህ አህመድ ሰይድ  እንደተናገሩት ህፃናትን የምንከባከባቸው እና ክፍተታቸውን የምንሞላላቸው ከሆነ  ባለ ሙሉ  ራዕይ መሆንንና  ለሌሎች በጎ ማድረግን ይማራሉ ፤ ለዪኒቨርሲቲው ሰራተኞችም ለዚህ ተምሳሌታዊ ድጋፋቸው ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል፡በመጨረሻም  ዶ/ር ወንድዬ አድማሱ እንደገለጹት  ዩኒቨርሲቲው እዚህ ቦታ ሲሰራ ትልቅ አላማ ተይዞ በመሆኑ  ውጭም ሆነ አገር ውስጥ የሚገኙ ምሁራን ጋር በጋራ በመስራት የአካባቢውና የአርሶ አደሩን ህይወት ለመለወጥ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን ብለዋል፡፡-ታህሳስ 24/2011

Leave a Reply

Your email address will not be published.