በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለአይነስውራን መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

በመቅደላ አምባ  ዩኒቨርሲቲ  መካነሰላም ካምፓስ  25 ለሚሆኑ  አይነስውራን  10 ቀን ያክል  መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና   ተሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሲቪክስ መምህርና የስልጠናው አዘጋጅ  መምህር ሰለሞን እሸቱ  እንደተናገሩት  የስልጠናው አላማ  አይነስውራን መሰረታዊ ኮምፒዩተርን  በመጠቀም  አቅማቸውን እንድያጎለብቱ  ለማስቻልና ዩኒቨርሲቲውም በሚሰጠው ማህበረሰብ አገልግሎት አካል ጉዳተኞችን መሰረት አድርጎ እንድሰራ ለማበረታታት  ነው ብለዋል፡፡

የስልጠናው ይዘትምአይነስውራን ኮምፒዩተርን በመጠቀም  መፃፍ፣ማንበብ፣ኢንተርኔትን መጠቀምና በመደበኛ ሁኔታ መረጃን በመለዋወጥ  ተግባቦታቸውን ለመጨመር  መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

 የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት አቶ አስማማው ምስጋናው  እንደተናገሩት  ስልጠናው  ከብሬል ባለፈ  ከሌላው  ማህበረሰብ ጋር እንድንግባባ የሚያስችለን በመሆኑ  ዩኒቨርሲቲው ያደረገልን እገዛ  ትልቅና ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም መምህር ሰለሞን እሸቱ  ባስተላለፉት መልዕክት  የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት የስልጠና ፕሮፖዛለቸውን ተቀብሎ  ስልጠናው እንድሰጥ በማድረጉ ና ሌሎች 9 መምህራንም ከሳቸው ጋር በመሆን እገዛ ስላደረጉላቸው  አመስግነው በቀጣይም እንድህ አይነቱ ተግባር መቀጠል እንደሚገባው  ተናግረዋል፡፡ሚያዚያ 8/2011 �3� �w

Leave a Reply

Your email address will not be published.