በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በ2.3 ቢሊዮን ብር የሚገነባውን የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ አፈፃፀም በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ምልከታ ተካሄደ፡፡

Latest News

(ታህሳስ 25/2016 ዓ..ም የህዝብና አለማቀፍ ግንኑነት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በሁለቱም ግቢዎቹ የተጀመረው የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ አፈጻጸም አስመልክቶ በቱሉ አውሊያ ዋናው ግቢ እየተገነባ የሚገኘውን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የግንባታው መሀንድሶች እንድሁም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በተገኙበት ምልከታ ተካሂዷል ፡፡በግንባታ ቦታው ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ሰዋአገኝ አስራት (ዶ/ር) ግንባታው በ2.3 ቢሊዮን ብር የሚገነባ መሆኑን ገልፀው ሲጠናቀቅ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚቀርፍ እንደሆነ አስረድተው ሆኖም በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ የበጀት ችግር ማነቆ መሆኑንም አስረድተዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.