በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ብዝሀነትና እኩልነት ለሀገር አንድነት›› በሚል መሪ ሀሳብ  የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡

Latest News

(ህዳር 20/2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት)

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ምክኒያት በማድረግ ህዳር 20/2016 ዓ.ም የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት  ሰውአገኝ አስራት (ዶክተር) እንደተናገሩት ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ መገለጫዎች ያሏቸው  ከ80 በላይ ብሄሮች ያሉባት ሀገር በመሆኗ የምንከተለው  የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት መሆኑን ገልፀው  የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት ግንባታ በተስተካከለና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከሄደ ለሰላም ግንባታ ዋና መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡

በፓናል ውይይቱም  ፌደራሊዝምና የፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ  እንድሁም ብሄር ብሄረሰቦችና የሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ  በሚል አርዕስት በመምህር መሀመድ ኢብራሂምና በመምህር አብርሃም በቀለ የውይይት የመነሻ ጽሁፍ  ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡

በቀረበው የመነሻ ፅሁፍ ላይ አሰተያየቶችና ጥያቆዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ማደማደሚያ ከመድረክ ተሰጠ ሲሆን ውይይቱም ለሀገር ግንባታ ስርዓቱ ግብአት  ከመሆኑም ባሻገር ግልፀኝነትን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.