በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በተካሄደ የአሰራር ስርዓት ጥናት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

Latest News

ህዳር 14/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክሬት

የአሰራር ስርዓት አንድ ስራ ሲከናወን ስራውን ለመፈፀም የተቀመጡ ሂደቶችን፣አዋጆችን፣መመሪያዎችን፣ፈጻሚ አካላትንና በመካከላቸው ያለውን የስራ ግንኙነት የሚያመላክት ስርዓት ሲሆን የተካሄደው ጥናት አስፈላጊነትም በዩኒቨርሲቲው ከአሰራር ስርዓቶችና ሂደቶች መካከል ለሙስና ክፍተት የሚፈጥሩትን በመለየትና በማጥናት ወንጀልና ብልሹ አሰራሮችን ለመካለከል መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልፀዋል፡፡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰው አገኝ አስራት (ዶ/ር) እንደተናገሩትም የአሰራር ስርዓት ጥናቶች እየተሰሩ ለውይይት መቅረባቸው አስተማሪና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በውይይቱም የአሰራር ስርዓትን በተመለከተ አጭር ሰነድ በአቶ መሀመድ ፈንታው የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ና በተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ዘርፎች ዙሪያ የተደረጉ የአሰራር ስርዓት ጥናት ዙሪያ በአቶ ገብረሃና የኋል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ባለሙያው ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸው በጥናቱ የተመላከቱ የአሰራር ችግሮች ማስተካከያ እንድደረግባቸው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡የቀረበው የአሰራር ስርዓት ጥናት የሚታዩ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በመለየት ሊከሰቱ የሚችሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚኖረውና በቀጣይም ይበልጥ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ የስራ ክፍሎችን የአሰራር ስርዓት ጥናት በማድረግ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አቶ መሀመድ ፈንታው አስገንዝበዋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.