በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ስራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

Latest News

(ጥር 27/2016 ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት )

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በቱሉ አውሊያ ዋናው ግቢ የሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች በግቢው አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ዙሪያ ወይይት አካሂደዋል ፡፡የውይይቱ ተሳታፊዎች በውይይታቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ፤የባለሙያ ዕጥረት መኖር ፣ የመብራት መቆራረጥ፣ በጋራ ተቀናጅቶ ከመስራት ይልቅ በተናጠል ጥረት ማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ እርካታ እንዳይኖር እንቅፋት እንደሆነባቸው አንስተዋል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የአስተዳዳርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ሰው አገኝ አስራት(ዶ/ር ) ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ‹‹የአስተዳደር ዘርፉ ከአካዳሚክ ዘርፉ ጋር በመቀናጅት የአገልግሎት ጥራት በማምጣት የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ በመናበብ መስራት ወሳኝ እንደሆነ አሳስበዋል ፡፡ የተነሱ ችግሮችም በአጭር ጊዜ መፍትሄ የሚሰጣቸው እንደሆኑ አክለው ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.