በመካነሰላም ካምፓስ በምርምር ውጤቶች ላይ ዳሰሳ ተካሄደ ::

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤትከ2011-2013 ዓ.ም ድረስ ደረጃቸውን ጠብቀው በማለፍ ወደ ተግባር የተሸጋገሩ 23 የምርምር ትልሞችን ትግበራና ያስገኙትን ተጨባጭ ውጤት በ17/07/2014 ዓ.ም በመካነሰላም ግቢ በዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና ተግባራዊ ልምድ ባላቸው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ናሌሎች የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ ባለድርሻዎች በተገኑበት አስገምግሟል ፡፡የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ፡ በዚህ የውጤት ዳሰሳ መድረክ ላይ የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝምና የግብርና መምሪያ ሀላፊዎች፣ የወረዳ ባህል ቱሪዝም ፣ ትምህርትና ሴቶች ህጻናት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ሙያተኞች እንዲሁም የሚመለከታችው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሰራተኞችን ማሳተፉ ከዳሳሳ ግምገማው ማግስት ወደ ማህበረሰቡ በማድረስ ምርመሮቹ ችግር ፈች ለማድረግ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡የጥናትና ምርምር ትልሞች ትግበራና ያስገኙት ውጤት ዳሰሳ መድረክ በሁለቱም ግቢዎች የተከናወነ ሲሆን በዋናው ግቢ ቱሉ አውሊያ በመጀመሪያው ዙር የግብርናና የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ፣ ተገምግሟል ፡፡ በሁለተኛው ዙር በመካነሰላም ግቢ ደግሞ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በስነሰብና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተከናወኑ የምርምር ውጤቶችን የሚዳሰስ 23 የምርምር ውጤቶች ቀርበው ግምገማ የተደረገ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር አገኝ ሽበሽ ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.