በምርምሩ ዘርፍ ለተሰማሩ መምህራን በጥናትና ምርምር ስነ ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመተባባር ለ2ኛ ዙር በዘርፉ ልምድ ባላቸው አንጋፋ ምሁራን በምርምሩ ዘርፍ ለተሰማሩ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ መምህራን በጥናት ምርምርና ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አማካኝነት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና (Training for Enhancing the knowledge and skills of University Research ethics and Project writing ) በሁለቱም ግቢዎቹ ለተከታታይ 3 ቀናት እየተሰጠ የነበረው ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰው አገኝ አስራት ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት <<ልምድ ባላቸው ምሁራን ከላን እውቀት ላይ በመጨመር የጥናትና ምርምር ስራችንን በጥራት በመስራት የአካባቢያችንን ብሎም የሀገራችንን ችግር ለመፍታት በበቂ እቀውቀትና ክህሎት እንዲሁም ስነ- ምግባር ጭምር ተላብስን እንድሰራ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረው>> በቀጣይም በአጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና የመምህራን አቅም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አክለው ተናግረዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ አበበ ምስጋናው በበኩላቸው ከአንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልምድ ባላቸው ምሁራን የምናገኘውን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ፡ከራስ አልፎ ለማህበርሰቡ ፣ከማህበረሱ አልፎ ለሀገር ችግር የሚፈታ የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ፤የቴክኖሎጅ ሽግግር ስራ እንድንሰራ በር የሚከፍት በመሆኑ የተገኘውን እውቀትና ልምድ ፈጥኖ ወደተግባር በመቀየር መስራት እንደሚጠበቅ አሰረድተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.