ታህሳስ/ 2015 ዓ.ም (የመቅደ አምባ ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመትን አባላት፣ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው ከተሰበሰበ ገንዘብ መካነ ሰላም ከተማ ፣ጊንባ ከተማ እና ለጋምቦ ወረዳ ከወለጋና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ተፈናቅለው በመጠለያ በችግር ላይ ለሚገኙ 751 ተፈናቃዮች 563250 ብር ድጋፍ ተደርጓል ።የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር አቶ አረጋ ሊበን በገነቴ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን በቀጥታ በችግር ላይ ለሚገኙት ወገኖች ባሰራጩበት ወቅት እንዳስታወቁት በሀገራችን በተፈጠረው የሰላም ችግር ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በመካነ ሰላም ከተማ ፣ ጊንባ ከተማ እና ለጋምቦ ወረዳ በመጠለያና ከአርሶ አደሩ ጋር ተቀላቅለው በከፋ ችግር ላይ ለሚገኑ 751 ተፈናቃዮች ‹‹563250›› ብር ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል ፡፡ ድጋፉ የተገኘው ከዩኒቨርሲቲ ማኔጅመትን አባላት፣ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች በ2014 ዓ.ም ከውሰኑት የአንድ ወር ደመወዛቸ የተሰበሰበ እንደሆነም አክለው ተናግርዋል ፡፡በለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ በመጠለያ ካምፕ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የተፈነቃዩብዛት ከፍተኛ ቢሆንም የከፈ ችግር ያለብንን በመለየት ‹‹ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላደረገልን የብር ድጋፍ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦
website- https://mkau.edu.et/
fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University
twitter- https://twitter.com/mekdela_amba
LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau
YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!





