ህዳር 3/2015 ዓ.ም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ባሉት 7 የምርምር ማዕከላት ለአካባቢው የአየር ንብረት የሚስማሙ የተለያዩ የሰብል ዝርያዎችና የጓሮ አትክልቶችን የማልመድ ስራ በመስራት ወጤታማ የሆኑትን ወደ ማህበረሰቡ በማሰራጨት የማስፋት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡በዚሁ መሰረት ወግዲ ወረዳ በሚገኘው የቱሉ አለንጌ የምርምር ማዕከል ያላመደውን ዞብል የተባለ የጤፍ ዝርያ ውጤታማ በመሆኑ በሁለት ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በክላስተር በማደራጀት ለቦረና ወረዳ 018 እና 019 ቀበሌዎች 80 ሄክታር መሬት እንድሁም በወገዲ ወረዳ 028 ቀበሌ 40 ሄክታር መሬት በጠቅላላው በ120 ሄክታር መሬት ላይ ለ173 በክላስተር የተደራጁ አ/አደሮች ዞብል የጤፍ ዘር በመስጠት የሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አገኝ ሽበሽ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡በወግዲ ወረዳ 018 ቀበሌ በክላስተር ተደራጅቶ ዞብል የጤፍ ሰብል ተጠቃሚ የሆኑት አርሶ አደር በላይ ሽፋው እንደተናገሩት ‹‹ ዩኒቨርሲቲው እዚሁ በወረዳችን በሚገኘው ምርምር ማዕከል ተሞክሮ ያቀረበልንን ዘር በክላስተር ተደራጅተን መዝራታችን ውጤታማ አድርጎናል፡፡ ሌሎች አርሶ አደሮች በተደጋጋሚ የእኛን ሰብል በመጎብኝት ለቀጣይ ዘሩን ለመጠቀም ፈላጎት እንዳላቸው ተናግርዋል ፡፡ እኔም ዘሩን ለሌሎች አርሶ አደሮች በመሰጠት የአርሶ አደሩ ትርፍ አምራችነት እንድጨምር እሰራለሁ ›› ሲሉ አክለው ተናግርዋል ፡፡




