በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት ገለጻ ተካሄደ፡፡

Latest News

የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት መስከረም 29/2015 ዓ.ም

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው ቺፎች፣ሱፐርቫይዘሮች፣ፈታኞች፣አንባቢዎች፣ፈተና ቆጣሪዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ስለ ፈተናው አሰጣጥ አጠቃላይ ሁኔታ ገለጻ ተካሂዷል፡፡በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ /ዶክተር/ በኦን ላየን ባስላለፉት መልዕከት ፈተናው በዚህ ሁኔታ መሰጠቱ አላማው በፈተናው ሂደት ሊያጋጥም የሚችልን ድካም መቀነስ መሆኑን ተናግረው ከስርቆት ነፃ የሆነ የፈተና ስርዓት እንድካሄድ አሳስበዋል፡፡የትምህርት ሚኒስቴሩ ብርሃኑ ነጋ /ፕሮፌሰር/ በበኩላቸው በተመሳሳይ በኦን ላየን ባስላለፉት መልዕከት ይህ ዘመቻ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ከሚሰሯቸው ዘርፈ ብዙ ሰራዎች አንዱ በሆኑን ገልፀዋል፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ታምሬ ዘውደ/ዶክተር/፣የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰው አገኝ አሰራት/ዶክተር /፣የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል /ዶክተር/ እና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት፣ ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አገኝ ሺበሺ/ዶክተር/ በፕግራሙ ላይ ተገኝተው የትውውቅና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.