አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሲስትም (IFRS) ስልጠና ተሰጠ፡፡

Latest News

ለዩኒቨርሲቲው የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል መምህንና እና ለፋይናንስ ሰራተኞች 22 ሰዎች አድሱ አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሲስትም (IFRS) ለ10 ተከታታተይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ስልጠናው ያስፈለገው ተቋማት በፊት ሲጠቀሙበት የነበረው አሰራር በመቀየሩ ከአድስ አበባ ዩነቨርሲቲ በመጡ መምህራን እንድሰጥ ማድረግ እንዳስፈለገ ተገልጿል።ከአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ የአካውንቲንግ መምህርና ስልጠናውን ሲስጡ ያገኘናቸው አቶ ታረቀኝ እንዳሉት ከዚህ ስልጠና የሚጠበቀው ውጤት ሰልጣኞች እራሳቸውን አብቅተው ተማሪዎችን በአድሱ ካሪኩለም መሰረት ማስተማር ይችላሉ እንድሁም ሌሎች የስልጠናና የማማከር ስራ መስራት ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡የመካነ ሰላም ካምፓስ አስተዳደርና የተማሪዎች ጉዳይ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተርና የአካውንቲንግና ፋይናንስ መምህር የሆኑት አቶ ባህሩ ገበየሁ በበኩላቸው እንደተናገሩት ስልጠናው በአግባቡ የተሰጠ በመሆኑ በተቀየረው ካሪኩለም መሰረት ተማሪዎችን ለማስተማር ያስችላል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.