‹‹አድስ እሳቤ ለቱሪዝም›› (Rethinking Tourism) በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡

History and heritage management Info Latest News

መስከረም 14/2015 ዓ.ም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትየመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል ዕውቀት ማስተባበሪያ ጋር በመተባበር የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ የስራ ሀላፊዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣ምሁራንና ፈፃሚዎች የተሳተፉበት መስከረም 14/01/2015 ዓ.ም ‹‹አድስ እሳቤ ለቱሪዝም›› (Rethinking Tourism) በሚል መሪ ቃል የአለም የቱሪዝም ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል ፡፡የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ ሀላፊና የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አገኝ ሺበሺ/ዶክተር/ እንደተናገሩት እለቱን አክብሮ ከመዋል ባለፈ ዘርፉ ለሀገራችን የስራ እድል ፈጠራና ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ በመሆኑ በሰፊው ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡ እለቱን በማስመልከት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የባህል፣ቅርስና ሀገር በቀል ዕውቀት ማስተባበሪያ እና ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ሁለት የዘርፉ ምሁራን የቱሪዝም ሀብትን የተመለከቱ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡የደቡብ ወሎ ዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን መኮነን በበኩላቸው እንደገለጹት ቅድሚያ ያሉትን የቱሪዝም ሀብቶች በማወቅ እነዚህን ሀብቶች የመጠበቅና ለቀሪው አለም ተደራሽ እንድሆን የማስተዋወቅ ስራ ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ ጌታሁን ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር በዩኒቨርሲቲያችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም የቱሪዝም ቀን እንድከበር ላደረጉ አከላት ምስጋና አቅርበው የቀረቡ የዳሰሳ ጥናቶችንና የቀረቡ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመውሰድ ዩኒቨርሲቲው የሚችለውን እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.