አድሶቹ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲም/ፕሬዝዳንቶች ከመምህራን ጋር የስራ ትውውቅ አደረጉ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ና የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት  ከግንቦት 13-14/2011 ከመምህራን ጋር የስራ ትውውቅና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር ስራ ላይ ሰፋ ያለ  ውይይት አካሂደዋል፡፡በውይይቱም ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የመምህራን ጥቅማጥቅም ያለመሟት ፣የተግባር ትመህርት ለመሰጠት የላብራቶሪ ማቴሪያል ያለመሟለት ና የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከል በዩኒቨርሲቲው የሸማቾች  ህበረት ስራ ማህበር አለመቋቋም የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

አቶ ኤሊያስ የአካዳሚክ ጉደዮች ዳይሬክተር  እንደገለፁት የተነሱት ጥያቄዎች ለውውታችን መነሻ  ጠቃሚ ሲሆኑ  ዩኒቨርሲቲው ችግሮቹን ለመፍታት ያላሰለሰ ጥረት  እያደረገ ይገኛል ፤ነገር ግን አሁን ያልተቀረፉ ችግሮችን ለይተን በመያዝ በቀጣይ  እንድስተካከሉ የጋራ ጥረት እናደርጋለን ሲሉ  ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ካሳ ሻወል በማጠቃለያው እንደገለፁት  በዩኒቨርሲቲው ሰፋ ያሉ ችግሮች ሊኖሩ ብን ይችላሉ፤ነገር ግን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታና ከዩኒቨርሲቲው አድስነት የተነሳ የማይሟሉ  ግአቶች ቢኖሩም  ችግሩን በጋራ ተባብረን በመስራት  ማቃለል ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም  በዩኒቨርሲቲው አቅም መፈታት የሚችሉ ችግሮችን ወስደን እናስተካክላለን ሲሉ ገልፀው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡     (ግንቦት 14/2011) a2���

Leave a Reply

Your email address will not be published.