“እቴጌ ጣይቱ የሴት መምህራን ማህበር” ተመሰረተ፡፡

Latest News

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ቱሉ  አውሊያ ካምፓስ  ህዳር  19/2012 ዓ.ም ሴት  መምህራን  ባደረጉት ስብሰባ  በጋራ ተወያይተው  የሴት መምህራን ማህበር መስርተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴት  መምህራን ስብሰባ አላማም የተጠናከረ  ማህበር ለመማቋቋም፣ሴት ተመራማሪዎችን ለማበረታታትና የሚቋቋመውን ማህበር  ስያሜ  ለመሰየም መሆኑ  የተገለጸ  ሲሆን   ማህበሩም  ‹‹እቴጌ ጣይቱ የሴት መምህራን  ማህበር››  ተብሎ  ተሰይሟል፡፡

የማህበሩ ሰብሳቢ  መምህርት ስዓዳ እንድሪስ እንደገለፁት “በሳይንስና ከፍተኛ  ትምህርት ሚኒሰቴር ሴት ተመራማሪዎችን የማበረታታት  ጅማሮ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ  በማህበረሰብ አገልግሎት፣በጥናትና ምርምር እንድሁም በቴክኖሎጅ  ማስፋፋት  ዘርፍ  በተቀናጀ  መልኩ  የእናቶችን  ችግር ሊቀርፍ የሚችል  ስራ  ለመስራት  ይህን  ማህበር ማቋቋም አስፈላጊ ሆኗል “ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ሴት ተማሪዎችን አቅማቸውን ለማሻሻል  በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት  በመታገዝ  የሴት ተማሪዎች በጎ አድራጎት ክበብ  ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙም  ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ሴቶች በብዙ መልኩ መታገዝ ያለባቸው መሆኑን ተረድተው  የዚህን ማህበር መመስረት ሀሳብ  ላፈለቁት ዶክተር ካሳሁን አህመድ  ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

                                                       ህዳር 23/2012

Leave a Reply

Your email address will not be published.