እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!

Info Latest News

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በታታሪና ቁርጠኛ አመራሮቹ፣ መምህራኑ፣ ሰራተኞቹ እና ተማሪዎቹ ባለፉት ተከታታይ 4 አመታት በርካታ መሰናክሎችን በቀናት እያለፈና ወርቃማ ስኬቶችን እያስመዘገበ መምጣቱን ሁላችንም የምናውቀው ገሀዳዊ ሀቅ ነው።የሳይንስና ክፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር፣ የመማር ማስተማር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር አፈጻጸም ውድድር ላይ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲያችን ከ22ቱ የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መስፈርቶቹን አሟልቶ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ሽልማት አንስቷል።ክቡራንና ክቡራት ዩኒቭርሲቲያችን አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች !! ዩኒቨርሲቲያችን እንደ ወትሮው ሁሉ በአጭር ጊዜ ታሪክ መስራት መጀመሩን በዚህ ታላቅ ሀገራዊ መድርክ ላይ አንጸባራቂ ድል በመቀናጀት አብስሮናልና እንኳን ድስ አለን!! እንኳን ደስ አላችሁ!!ክቡራንና ክቡራት !!ይህ ወጤት የመላ ዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ድምር ጥረት ውጤት በመሆኑ ሁሉም ሊኮራና ባስገኘው ስኬት ሊበረታታ ይገባዋል። ዩኒቨርሲቲያችን ስኬታማና ታሪካዊ ጉዞውን ገና ጀመረ እንጂ አልጨረሰም፡፡ ስለሆነም እንደውትሮው ሁሉ የሚገጥሙንን ችግሮች በጽናትና በቁርጠኝነት እያለፍን ነገም ከዚህ ለበለጠ ስኬት መረባረብ እንደሚጠበቅ ዩኒቨርሲቲው መልእክቱን እያስተላለፈ በድጋሜ እንኳን ደስ አለን ይላል!ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦website- https://mkau.edu.et/fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.Universitytwitter- https://twitter.com/mekdela_ambaLinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mauYouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን! ሃምሌ 8/11/2013 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.