‹ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ ደምን ለግሶ ህይወት ማዳን ነው› በሚል መርህ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱም ካምፓሶች የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

Latest News Research news

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ቱሉ አውሊያ መካነሰላም ካምፓሶች የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሰራተኞች፣መምህራን፣ ተማሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ  የተሳተፉበት3ኛው ዙር የአንድ ቀን ለህዝቤ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

የደም ልገሳ ፕሮግራሙ በዋናው የቱሉ አውሊያ ካምፓስ  ከጥር ሰላሳ  እስከ የካቲት ሁለት 3 ተከታታይ ቀናት  የተካሄደ ሲሆንከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ  78 ተሳታፊዎች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ደግሞ 9 ተሳታፊዎች በጥቅሉ 87 ሰዎችም ደም ለግሰዋል፡፡በተጨማሪም በመካነሰላም ካምፓስ ከየካቲት 3 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም 26 ተሳታፊዎች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ  ደም የለገሱ ሲሆን በአጠቃላይ በሁለቱም ካምፓሶች 113 ሰዎች ደም ለግሰዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የበጎ አድራጎት ስራዎች አስተባባሪ ኮሚቴ  ሰብሳቢና የሲቪክስ መምህር የሆኑት አቶ ኢሳ መሀመድ እንደተናገሩት በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ወቅትየተማሪች ተሳትፎ በጣም እንዳስደሰታቸው ገልፀው ይህን  አይነቱን የበጎነት ትልቅ ማሳያ ተግባር ለማስቀጠል ተከታታይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

አቶ አንዷለም በላይ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ዳይሬክተርም  በበኩላቸው እንደገለፁት የመቅደላ አምባ  ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ከአሁን በፊትበአንድ ቀን ለህዝቤፕሮግራሙ  በቱሉአውሊያ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ያከናወነ መሆኑን በኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች የዩኒፎርም ልገሳ ማድረጉን አስታውሰው  የደም ልገሳ ፕሮግራሙም የዚሁ  አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ በጎ ተግባር በመሳተፍ ደም የለገሱ ተማሪዎች በበኩላቸው  ለዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች በሰጡት አስተያየትደም በማጣት ምክኒያት ብዙ እናቶችን እያጣናቸው በመሆኑ ህይወት እንዳዳንንስለሚሰማን ደም በመስጠታችን የሚሰማን ደስታ የላቀ ነውብለዋል፡፡
                                            -የካቲት 11/2011 ?=���w

Leave a Reply

Your email address will not be published.