ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አደረጉ!

Latest News

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ሀይል ሀገርን ለማፍረስ፣ሀብትና ንብረትን ለማውደምና ለመዝረፍ ብሎም በዜጎች ላይ ፈረጀ ብዙ ቀውሶችን ለመፍጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጉ በሁላችንም ዘንድ የሚታወስ የቅርብ ጊዜ ሁነት ነው፡፡ በዚህ ወራሪና ዘራፊ ቡድንም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከብር 1.2 ቢሊየን በላይ የሆነ ሀብትና ንብረት ማጣቱ በተደረገው ጥናት ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ምስጋናና ክብር ለተባበሩት የሀገራችንና የክልል የፀጥታ ሀይሎች ይገባቸውና በዚህ የእናት ጡት ነካሽ ሀይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች በከፍተኛ ሽንፈት ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡በመሆኑም ፈርሰን፣ወድመን እና ተስፋ ቆርጠን እንድንቀር የማድረግ ህልምና እቅዳቸው እንዳልተሳካ በአንድነትና በጋራ ትግላችን በተግባር የሚታዩ ሰራዎችን በመሰራት የመላ ኢትዮጵያውያን ልጆች የዕውቀት ማዕድ፣ የከህሎት ማሻሻያ፣ የሳይነስና የቴክኖሎጂ ሽግግር መፍጠሪያ ከሆኑት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነውን መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ወደ ስራ ለማሰገባት የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡በዚህም ሂደት ዩኒቨርሲቲው ከደረሰበት ክፍተኛ ጉዳት በአጭር ጊዜ አገግሞ ሀገራዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ ለማስቻል በሀገራችን ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከአራቱም አቅጣጫዎች እቦታው ድረስ በመምጣት የዩኒቨርሲቲውን ክፍተት የሚሞሉ ግብአቶችን በአይነት በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡በዚህም መሰረት ይህ ዜና እስከ ተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግምታቸው ከብር 1.6 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ኮምፒውተሮችን፣ኦዳ ቡልቱ ዩኒቨርሲቲ ግምታቸው ከብር 1 ሚሊየን በላይ የሆኑ ኮምፒውተር፣ፕሪንተርና የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግምታቸው ብር 922,520 የሆኑ የተማሪዎች ምግብ ማብሰያና ማቅረቢያ ቁሳቁሶችን፣ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግምታቸው ከብር 12 ሚሊየን በላይ የሆኑ በርካታ ቁሳቁሶችን፣ ድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ ግምታቸው ብር 1.8 ሚሊየን የሆኑ ልዩ ልዩ ግብአቶችን ደግፈዋል፡፡በዚህ አጋጣሚም ዩኒቨርሲቲውን መልሶ ለማቋቋምና ወደ ስራ ለማስገባት በሚደረገው ሂደት ፈጣን ምላሽ ለሰጡን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ይህንንም ላስተባበሩ አካላት ሁሉ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም ታላቅ ምስጋና ማቅረብ የምንወድ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትየካቲት 01/2014ዓ.ም ጊምባኢትዮጵያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.