የለጋምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የችግኝ ዝርያዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡

Latest News

የለጋምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከአቀስታ ችግኝ ጣቢያ ከ10 ሽህ በላይ የተለያዩ የችግኝ ዝርያዎች ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክትር ካሳሁን አህመድ በተገኙበት አስረክበዋል ፡፡ዶክተር ካሳሁን አህመድ ችግኙን በተረከቡበት ወቅትም ወረዳው በተለያ ጉዳዮች ድጋፍ በጠየቅነው ሁሉ እንደሚያግዝ ገልጸው ግብርና ጽ/ቤት ከራሱ ቀንሶ ስለሰጠን ለተደረገው ድጋፍም ከፍያለ ምስጋና አለኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አስተራየ መንገሻ በበኩላቸው በጊቢያችን በያዝነው ክረምት ከ20ሽህ በላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች የተዘገጁ በመሆኑ የተደረገው ድጋፍ እቅዳችንን ለመሸፈን እንደሚያግዝ ገልጸው በቀጣ የግቢው ማህበረተሰብ በተሳተፈበት እንደሚተካል አስታወቀዋል ፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube-https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEA ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ሃምሌ 5/2013 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.