የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ለአድስ ገቢ የ1ኛ አመት ተማሪዎች የህይዎት ክህሎት ስልጠና ሰጠ

Latest News

የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ለአድስ ገቢ የ1ኛ አመት ተማሪዎች  በሁለቱም ግቢ ከጥቅምት 22 እሰከ 23/2012 ለሁለት ተከታታይ ቀናት የህይዎት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል ፡፡  በስልጠናው በሁለቱም ግቢ 2094 አድስ ገቢ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን ውጤታማ ለመድረግ  39 የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን  በአሰልጣኝት ተሳትፈውበታል፡፡ስልጠናው ትኩረት ያደረገበት ርዕሰ ጉዳይ ፡- በጥናት ክህሎት ፤ በመግባባት ክህሎት ፤ሀሳብን በነጻ መግለጽክህሎት  ፤ ጭንቀትን ስለመቆጣጠር ፤የአቻ ግፊትን ስለመቋም  እና በስነ- ተዋልዶ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ  ያተኮረ ነበር፡፡         የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ሸጋው መኮነን እንደገለጹት  ዩኒቨርሲቲው ለአድስ ገቢ ተማሪዎች ይህንን የህይወት  ክህሎት ስልጠና ሲሰጥ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በሙያው የተሸሉ  የአሰልጣኝ ስልጠና የሚሰጡ 5 መምህራን በማምጣት ለ39 አሰልጣኞች ስልጠናውን እንድሰጡ  በማድረግ   አድስ ገቢተማሪዎችን አከባቢውን እንዳውቁና እንድላመዱ ከማድረግ ባሻገር  የሚጠቅሙና ያማይጠቅሙትን እኩይ ተግባራት እንድለዩ አቅም የሚፈጥር ስልጠና እንደሆን ተናግረዋል ፡፡በመካነሰላም ካምፓስ ስልጠናውን እየሰጡ ያነጋገርናቸው መ/ርት ቅድስት ቢያዝን በበኩላቸው  ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በአድ ስ ለሚመጡ ተማሪዎች  ከውጭ ይዘውት የመጡትን አስተሳሰብ በመቀየር አድስና የተስተካከለ አላማ እንድኖራቸው ያስችላል ሲሉ  ለመቅዳአምባ ዩኒቨርሲቲ የኩሙኒኬሽን ጉ/ዳርሬክቶሬት ዝግጀት ክፍል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

                   ጥቅምት 24/2012

Leave a Reply

Your email address will not be published.