የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ትልሞችን አስገመገመ ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንትጽ/ቤት የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንድሁም የቴክኖሎጅ ሽግግር የጥናት ትልሞችን ከወሎ ፣ከወልድያ፣ ከደብረብርሃን ፣ከባህርዳር ፣ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች እንድሁም ከሲሪንቃ ግብርናናና ከአንዳሳ ላይፍ ስቶክ ምርምር ማዕከላት የውጭ ገምጋሚ ምሁራንን በመጋበዝ ከታህሳስ 4-5 /2012 ዓም ለሁለት ተከታታይ ቀናት አስገምግሟል ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን አህመድ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የተቋቋመባቸውን ሶስት ዋና ዋና አላማዎች ማለትም መማርማስተማርን ፣ ጥናት ምርምርን እና የማህበረስብ አገልግሎትን በተሳካ መልኩ ለመፀም 41 የጥናትና ምርምር፣35 የማህበረሰብ አገልግሎት፣4 የቴክኖሎጂ ሽግግር በ”ድምሩ 80 ትልሞች ቀርበው ልምድ ባላቸው የሙያው ባለቤቶች ተገምግመው ውሳኔ ያገኛሉ ብለዋል፡፡ መምህራን ከማስተማር ስራቸው ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ችግሮች በጥናት መለየትና መፍታት እንዲችሉ ልምድ ያላቸውን ሙህራን ከነባር ዩኒቨርሲቲዎች በመጋበዝ የተሰራውን የጥናት ትልም ማስገምገማችን ለተመራማሪዎች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም በንግግራቸው ጨምረው ገልፀዋል ፡፡ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በገምጋሚነት የተሳተፉት መምሀርት ዘቢባ መንግስቱ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ሊሰራቸው ያቀዳቸውና ለግምገማ የቀረቡት የጥናት ትልሞች ልምድ ባላችው ሙህራን መገምገማቸው ሳይንሳዊ ከመሆኑም በላይ የሚጠኑትን ጠናቶች ወደ ተግባር ለማስገባት ለተመራማሪዎች አቅም የሚፈጥር ግብት የሚሰጥ ነው ብለዋል ፡፡ በተመሳሳይ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በገምጋሚነት የተስተፉት ዶ/ር እሸቱ ሰይድ በበኩላቸው እስካሁን በነባር ዩኒቨርሲቲዎች ያልተለመደና የጀማሪ ተመራማሪዎችን አቅም ለማሳደግ እጅግ ጠቃሚና አስተማሪ የሆነ ተግባር መሆኑን ገፀው የጥናት ትልሞቹ ልምድ ባለቸው ምሁራን እውቅና አግኝተው ወደ ተግባር ሲገቡ ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ በተግባር ለማወል ያስችለዋል ሲሉ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዝግጅት ክፍል አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.