የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ዩኒቨረሲቲው ባቀፋቸው 12 የምራብ ወሎ ወረዳዎች፣ የሁለት ከተማ አስተዳደር ፖሊሶች ፤ አስተዳዳር ጸጥታ ና ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እንድሁም ከደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ና አስተዳደር ጸጥታ ሀላፊዎች ያከተተ ከየካቲት 6-7/6/2012 ለሁለት ተከታታይ ቀን ለ192 ሰልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል ፡፡ ሰልጠናውም በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጉዳይዮች ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልገሎት ፤የሰው መግደል ወንጀል ፤የሰብአዊ መብትና የሀይል አጠቃቀም ፤ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ፤ የደቦ ፍርድ ና የፖሊስ ስነ-ምግባር የሚሉት ያከተተ ነበር፡፡ በስልጠናውም ወቅት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውደ እና የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማደር ለማ ተስፋየ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስነ- ስርዓት አካሂደዋል ፡፡ 
የዩኒቨረሲቲው ጥናት ምርምር ና መህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን አህመድ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ‘’ዩኒቭረሲቲው የማህበረሰቡ ፤ማህበረሰቡ የተቋሙ’’ በሚል መሪቃል ያነገበውን አላማ ለማሳካት በዞናችን በማህበረሰቡ የሚደረሱ የተለያዩ ወንጀሎችና ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ለመቀነስና የዩኒቨረሲቲውን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር የዩኒቨረሲቲው ማኔጀመንት ለጉደዩ ትኩረት በመሰጠት በሁለት ዙር የሚሰጥ ሰልጠና ፈቀዱዋል ፡፡ስለሆነም ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና ማግስት የተሰጡትን ስልጠና እንደ አቅም በመጠቀም ወንጀልን የበለጠ እንደሚከላከሉ አምናለሁ ሲሉ ገልጸዋል ፡፡የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማደር ለማ ተስፋየ በበኩላቸው እንደገለጹት ‘’በዞናችን ምዕራባዊ ወረዳዎች የሚታዩ የወንጀል መበራከቶችን ለመቀነስ በተለይ የደቦ ፍትህ ፣ አስገድዶ መድፈር ላይ ወንጀል ጠል ማህበረሰብ ለመፍጠር ያስችል ዘንድ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ማኔጀመን የሰጠው ትኩርት ከፍተኛ በመሆኑ እድሉን ተጠቅመን ህብረተሰቡን ወንጀል ጠል እንድሆን ፖሊስ ኦፊሰሮቻችንና አመራሮቻችን ይሰራሉ” ሲሉ ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽንጉ/ዳይሬክቶሬት ዝግጅት ክፍል አሰተያየተዎን ሰጥተዋል ፡፡
የካቲት/2012ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.