የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

Latest News Research news

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊና የመጀመሪያ የሆነው እና ከፌድራል፣ከዩኒቨርሲቲዎች፣ከአማራ ክልል እንድሁም ከደቡብ ወሎ ዞንና ዩኒቨርሲቲው ከሚያቅፋቸው 11 ወረዳዎች የተወጣጡ ከ150 በላይ የሆኑ ባለድርሻና አጋር አካላት የተሳተፉበት አውደ ጥናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ቱሉ አውሊያ ሰኔ 14/2011 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በአውደ ጥናቱም አስትራቴጅካዊ አጋርነት ለላቀ ጥናት  ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በሚል መሪቃል በዩኒቨርሲቲው የትኩረት አቅጣጫዎች ማለትም በመቅደላ አምባ ታሪካዊ ቦታ መልሶ ማቋቋም፣በቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክና በበቶ ወለቃ አባይ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርኮችን ከጥፋት የማዳን እንድሁም በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ የጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የቀጣይ አጀንዳዎች ዙሪያ ከ150 በላይ ለሚሆኑ ከፌድራል፣ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ከአማራ ክልል፣ከደቡብ ወሎ ዞንና የወረዳ አመራሮች እንድሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ የተወጣጡ አካላት በተገኙበት 8 የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በነዚህ ጥናታዊ ጽሁፎችም ታሪካዊ፣ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በመመዝገብ፣ በመጠበቅና በማበልጸግ ጭስ አልባ ኢንዱስትሪውን የማሳደግ ፤የካባቢው ችግር በዳሰሳ ጥናት እየተለየ የተራቆተውን አካባቢ መልሶ የማልማትና ምርታማነትን የመጨመር እንድሁም የስራ ፈጠራን ማሳደግ የሚሉ ጭብጦች  ተነስተው  መፍትሄ የተመላከተ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ፕሮግራም እየተዘጋጀ የሚዳብር መሆኑ ተገልጸዋል፡፡

በመጨሻም የጥ/ም/ማ/አገ/ም/ፕ/ጽ/ቤት ባደረገው የማጠቃለያ ግምገማ አውደጥናቱ የተቀመጡለትን አላማዎችና ግቦች ያሳካ እንደነበርና ለዚህም  የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና አመራሮች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ሃላፊነታቸውን መወጣታቸው ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ተገልጾ በቀጣይም ሰራተኛውና አመራሩ ተናቦና ተደጋግፎ መስራት ከቻለ ታላላቅ ፕሮግራሞችን ማካሄድ እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደበት ዝግጅት መሆኑን ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡                                               ሰኔ 28/2011

Leave a Reply

Your email address will not be published.