የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራና የስራ አፈላለግ ስነ-ዘደ ስልጠና ሰጠ፡፡

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የደሊቨሮሎጅ ዳይሬክቶሬት ነሀሴ 21 በ2014 ዓ.ም በመደበኛው መርሃ ግብር ለ3ኛ ዙር ለሚመረቁ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ከ17-19/2014 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ያክል የስራ ፈጠራና የስራ አፈላለግ ስነ-ዘደ ስልጠና ሰጥቷል፡፡የዩኒቨርሲቲው የደሊቨሮሎጅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ጋትራይ ቱት ስልጠናውን በንግግር ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በድግሪ ተምሮ መመረቅ የህይወት የመጀመሪያ ምዕራፍ እንጅ መጨረሻ ስላልሆነ ወቅቱን በሚመጥን ሁኔታ እውቀትና ክህሎታቸውን በየጊዜው እያሳደጉ መሄድ እንደሚገባቸው ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡የስራ ፈጠራ ስልጠናውን የሰጡት መምህር ፉአድ በሺር በበኩላቸው እንደገለፁት ሀገሮች ሀብታምና ደሃ የሆኑት ወይም በሀብታምና በደሀ ሀገሮች መካከል ልዩነት የተፈጠረበት ዋና ምክንያት የአመለካከት ልዩነት በመሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ተመራቂ ተማሪዎች የመንግስት ቅጥር ብቻ እንዳይጠብቁ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎች፦

website- https://mkau.edu.et/

fakebook- https://www.facebook.com/Mekdela.Amba.University

twitter- https://twitter.com/mekdela_amba

LinkedIn- http://linkedin.com/company/mekdela-amba-university-mau

YouTube- https://www.youtube.com/channel/UCqWmoX39VBK8Augft6tZiEAከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

ነሃሴ 19 /2014 ዓ.ም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published.