የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘመናዊ ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ የትጥበት አገልግሎት እንድሰጥ እያደረገ ነው፡፡

Latest News

ዩኒቨርሲቲው ቀደም ብሎ ኮሮናን ለመከላለከል ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ የተለያየዩ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ፣ የቫይረሱን መከላከያ ቁሳቁስ የማሰረጨትና የለይቶ ማቆ በመሆን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፤ አሁንም ተማሪዎቹን ለመቀበል ከሚያደርገው ዝግጅት ውስጥ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው ተመልሰው ሲመጡ በሚታጠቡበት ወቅት ንክኪ እንዳይፈጠር ከአቀስታ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ቴክኖሎጅውን ወደ ዩኒቨርሲቲው በማስገባት 16 ያክል ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ ዘመናዊ መታጠቢያ እያሰራ የሚገኝ ሲሆን ተሰርተው የተጠናቀቁት ለሰራተኛውም አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡የዩኒቨርሲቲው የጤና ክሊኒክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ እጅጉ እንደገለፁት ኒቨርሲቲው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ውስጥ ይህ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ መታጠቢያ መዘጋጀቱ የበሸታው ተጋላጭነትን በእጅጉ ይቀንሳል ያሉት ሃላፊው ስራው በተመረጡ በመግቢ በር ላይ፣በተማሪ መኖሪያ ዶርም፣በመማሪያ ክፍል፣በቤተመጻህፍት፣በተማሪዎች ክሊኒክ፣ በተማሪች መመገቢ አዳራሽና በቢሮዎች አካባቢ እድሰሩ እየተደረገ ሲሆን በቅርብ ቀን ውስጥ ስራው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.