የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 ዓ.ም አድስና ነባር ተማሪዎቹ ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም አካሄደ

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ  ለ2012 ዓ.ም አድስና ነባር  ተማሪዎቹ  በሁለቱም ካፓሶች  የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ዳይሬክተሮች ፣የስራ ክፍል ሃላፊዎች ፣ የመካነሰላም የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የለጋምቦና የቦረና ወረዳ አመራሮች፣የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የዩኒቨርሲቲው  ነባርና አድስ ተማሪዎች እንድሁም  ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ልዩ የእንኳን ደህና  መጣችሁ ፕሮግራም አካሄዷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው  ለእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ፕሮግራሙ  የወሎ ላሊበላ ባህል ቡድንን በመጋበዝ ለተማሪዎች ልዩ ልዩ መዝናኛዎችና አስተማሪ መልዕክቶች እንዲተላለፉ አድርገጓል፡፡

በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ታምሬ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክትም <<ዩኒቨርሲቲያችን በ2025 በኢትዮጵያ ካሉ ሶስት ግንባር ቀደምና ተመራጭ የ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ ሆኖ የመገኘት ራዕይ፣ ጥራቱን የተጠበቀና በምርምር የታገዘ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ የማፍራት፤በሀገራችን የልማት አቅጣጫና ፍላጐት ላይ ያነጣጠሩ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድና በውጤታቸውም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ እንድሁም የመንግሥትንና የህብረተሰቡን ፍላጐት ያማከለ የስልጠና፣ የምክር አገልግሎት በመስጠት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር የማድረግ ሶስት ቁልፍ ተልዕኮዎችን ቀርፆ ስራውን የጀመረ መኆኑን ገልፀው እንደ ማንኛውም ጀማሪ ተቋም የሚጋጥሙ ችግሮችን ሁሉ በትዕግስትና በቁርጠኝነት በማለፍና በማስተካከል ዩኒቨርሲቲያችንን መድረስ ወደሚገባው የከፍታ ደረጃ ለማድረስ የበኩላችሁን ያላሳለሰ ጥረት ላበረከታችሁ ሁሉ እያመሰገንኩ አድስ ተማሪዎቻንን እንደ ነባሮቹ ተማሪዎቻችን ሁሉ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያስተጓጉሉ ችግሮችን በፅናትና በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመታገልና በማስተካከል የዩኒቨርሲቲያችሁን የሰላም አየር አስጠብቃችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪየን ለማስተላለፍ እወዳለሁ >>ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡የዪኒቨርሲቲው ም/ል ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች አካላትም አጫጭር መልዕክቶችን ለተማሪዎች አስተላልፈዋል፡፡ u�Eg;����

የዩኒቨርሲቲው  አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳ ሻወል  እንደተናገሩት  ‹‹ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጣችሁ ተማሪዎቻችን የኛው እህቶችና ወንድሞች በመሆናችሁ በትምህርት ቆይታችሁ የተሳካ ጊዜ እንድኖራችሁ የምንችለውን ሁሉ  የምናደርግ ሲሆን በናንተ በኩልም የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ለማሳካት ለምናደርገው ጥረት ሁሉ ከጎችን በመቆም  አጋዥ እንድትሆኑ  አደራ››  ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዶክተር ካሳሁን አህመድ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት  በበኩላቸው‹‹ እንኳን ሜዳ ሙሉ እውቀት ከሞላበትና ከሚሸመትበት፣አንቱ የተባሉ የሃይማኖት ሊቃውንቶች ከበቀሉበትና ከሚበቅሉበት፣ግርማ ሞገስ የተላበሱ የሃገር ሽማግሌዎች ካሉበትና ከሚፈልቁበት ማማ፣በፍቅርና በገራገርነት ታጅበው አርሂቡ ማለት የዘወትር ተግባራቸው ከሆኑት እናቶቻችንና አባቶቻችን ምድር፣አብሮ የመኖር ልምድ ያካበቱ የፍቅር መኮንኖች የጀግኖች አምባና ታሪካዊ ቦታ እግዚያብሄር ይመስገን አልሃምድሊላሂ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በደህና መጣችሁ ››በማለት  የሚያነቃቃና አካባቢውን ገላጭ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው  የእስልምና፣የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችም  የእንኳን ደህና  መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ‹‹እዚህ አስከመጣችሁ ድረስ የኛው ልጆች ናችሁ›› በማለት ከማንኛውም መጥፎ ተግባር በመቆጠብ  አላማቸውን እድያሳኩ  ምክር የለገሱ ሲሆን ለዚሁም ድጋፋቸው እንደማይለያቸው ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.