የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ሊተገብሩ የሚገቧቸውን እና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::

Latest News

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሪጂስትራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር አብርሃም በለጠ እንደገለጹት በዚህ ዓመት ለዩኒቨረሲቲውየተመደቡልንን ተማሪዎች መዝግበን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት አድርገን የጠበቅን ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ለተማሪዎቻችን አጠቃላይ መረጃ የሚሆን የስነመግባርና የድሲፕሊን መምሪያ ዙሪያ ፣የሬጅስትራር አሰራር መመሪያዙሪያና የኮሮና ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አድስገቢ ተማሪዎች ወደ መማርማስተማር ስራው ለማሸጋግር ነው ብለዋል ፡፡የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነጋ ከሰተ በበኩላቸው አድስገቢ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ስራውን ከመጀመራችን በፊት ተማሪዎች ሊተገብሯቸው የሚገባቸውንና የተከለከሉ ተግባራት የማስተዋወቅ ስራመሰራቱ በቀጣይ ቆይታቸው የተስተካከለ ስነምግባር ና የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ በማወቅ የመጡበትን አላማ አሳክተው ለመሄድ ወሳኝ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሰኔ 30/2013 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.