የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን በለጋምባ ወረዳ የሚገኝ የችግኝ ጣቢያ ስራዎችን ጎበኘ፡፡

Latest News Research news

በመቅደላ አምባዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ወንድየ አድማሱ የሚመራ የልዑካን ቡድን በለጋምቦ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ጋባዥነት በወረዳው ውስጥ የሚገኝ ችግኝ ጣቢያ ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

የጉብኝቱ አላማም ዩኒቨርሲቲው ላቋቋመውና ወደፊት ሊያቋቁም ላቀዳቸው የምርምር ችግኝ ጣቢያዎች ልምድ ለመውሰድና  ግብአት የማሰባሰብ ስራ ነው ሲሉ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንዷለም በላይ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ልኡካን ቡድን በበኩላቸው ካዩት የችግኝ ጣቢያ ልማት ጥሩ ልምድ እንዳገኙ ገልፀው ብዙ አይነት ፍራፍሬዎቸን ማልማት ላይ ውስንነት መመልከታቸውን እና በችግኝ ጣቢያው ውስጥበጥሩ ሁኔታ የለሙትም  ወደ አርሶ አደሩ  ማሰራጨት ላይ በስፋት እንዳልተሰራ  አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የለጋምቦ ወረዳ ግብርና           ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት  አቶ መሀመድ ጋሻውምእንደተናገሩት ከዩኒቭርሲቲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ሌሎች  ከወረዳው ግብርና ጽቤት የመጡ አካላት ለአርሶ አደሩ የሙያ ክህሎት ስልጠና እና የማቴሪያል ድጋፍ እንድያድርግ  ዩኒቭርሲቲውን ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም ዶክተር ወንድዪ አድማሱ በሰጡት አስተያየት ዩኒቨርሲቲው በጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው ወረዳዎች ሁሉ የምርምር  ችግኝ ጣቢያ የመመስረት እቅድ  እንዳለውና የሚታየውን  የውሀ ችግር የመቅረፍ  ፣የመኖ ልማትን ማስፋፋት፣የዕፅዋት ሸፋንን የማሳደግ፣አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ላይ ተከታታይ ስራዎችን የማከናዎን፣የአርሶአደሩን ሰብል ምርታማነት የማሻሻል እና በአጠቃላይ  የተፈጥሮ ሀብትን የመመለስ ስራ እንደሚያከናውን ገልፀዋል፡፡

                                                                       -ጥር 1/2011 si�?�f��

Leave a Reply

Your email address will not be published.