የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ልዑክ ቡድን ታላቁን የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ ጎበኘ ፡፡

Latest News Research news

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ልዑክ ቡድን በቀን 15/02/2013 ዓ.ም መነሻውን መካነሰላም ካምፓስ በማድረግ ታላቁን የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ ጎብኝቷል፡፡የጉብኝቱ መሪ ቃልም ማወቅ ከማሳወቅ ይቀድማል!ማሳወቅ ማወቅን ይከተላል!አካባቢያችንን አውቀን እናሳውቅ! የሚል ሲሆን አላማውም አካባቢን በማወቅ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን፣ከማህበረሰቡ ጋር ቅርርብ በመፍጠር ችግሮችን መፍታት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ብሄራዊ ፓርኩ ከ1900-4280 ሜትር ከባህር ጠለል ባላይ ከፍታ ያለውና በ3 አይነት የአየር ንብረት ማለትም ደጋ፣ወይናደጋና ቆላ የተከፈለ ሆኖ 32 ወራጅ ወንዞችን፣10 የተፈጥሮ ዋሻዎችን፣ ከትልልቅ እድሜ ጠገብ የተፈጥሮ ዛፎች እስከ ትንንሽ ቁጥቋጦና የጓሳ ሳር፣30 አይነት የሚሆኑ የዱር እንስሳትን ከነዚህ ውስጥም 4 ብርቅየ እንስሳትን ማለትም ጭላዳ ዝንጀሮ፣የሚኒሊክ ድኩላ፣የስታርች ጥንቸልና ቀይ ቀበሮን ጨምሮ በርካታ የአዕዋፍ ዝርያዎችን አካቶ የያዘ ትልቅ ፓርክ ነው፡፡ በእለቱ ፓርኩን ሲያስጎበኙ የነበሩት አቶ ሰለሞን እንደተናገሩት ይህ ብሄራዊ ፓርክ የሀገራችንን ቅርሰ በማስተዋወቅ የሀገራችንንና የአካባቢውን ህብረተሰብ የአረንጓደ ኢኮኖሚ ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ ያለው ከመሆኑም በላይ ሰፊ የሆኑ የጥናትና ምርምር እንድሁም የቱሪስት መስህብ የሆነ የሀገር ሃብት መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ጠቁመው ለፓርኩ ትኩረት በመስጠት ያሉበትን የመንገድ መሰረተልማት ችግርና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነሰላም ካምፓስ ኢክስኪዩቲቭ ዳሬክተርና የልዑክ ቡድኑ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብዱረህማን አወል እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲው ልዑክ ቡድን ይህንን ለሀገር ትልቅ ፋይዳ ሊያበረክት የሚችል አስደናቂ ፓርክ መጎብኘቱ ፓርኩን ለምርምር ስራ በማዋል የዩኒቨርሲቲው አንዱ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ ወደ ፊት መሰራት ያለበትን በመለየት ከማህበረሰቡ ጋር ቅርርብ በመፍጠር ትልቅ ስራ የሚሰራበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.