የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የመስክ ምልከታና የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

Latest News

( ጥር 2016 የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት )

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ ከግቢ ውጪና በግቢው ውስጥ በተሰሩ ስራዎች ላይ ከተቋሙ ማህበረሰብና ከአካባቢው አጋር አካላት ጋር በመሆን ጥር 13/05/ 2016 ዓ.ም የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡በመስክ ምልከታው ከተካተቱት ቦታዎችም ከግቢው ውጭ በአጥሩ ዙሪያ ያሉ ንብረትነታቸው የዩኒቨርሲቲው የሆኑ የልማት መሬትና በግቢው ውስጥ ደግሞ ከተጎበኙት የስራ ክፍሎች መካከል እንደ ህጻናት ማቆያ፣ለሀብት ማመንጫነት የሚውል የከርሰምድር ውሃ ቁፋሮ፣የስማርት ክላስ ሩም፣ የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ፣የድጅታል ላይብረሪ፣ የእንስሳት እርባታና የህትመት ክፍል ግንባታ ፕሮጀክቶችን አካቷል፡፡ከመስክ ምልከታው በኋላም በተካሄደው አጭር የምክክር መድረክ ላይ ውስንነቶችን በመቅረፍና የታዩ ጥሩ ተሞክሮዎችን በማስቀጠል ለማህበረሰቡ የሚውሉ ልማቶችን በጋራ በመስራት ሰላማዊና ልማታዊ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ በጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.