የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ግቢ የዕለት ምግብ ለሌላቸው ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

Latest News

(ጥር2016ዓ.ም የህዝብና አለም አቀፍግንኑነት)

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈች ምርምር ፣ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የማህበረሰብ አገልግሎት እንድሁም ጥራት ያለው መማር ማስተማር ተልኮውን ለመወጣት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ በዚሁ መሰረት ከተለያዩ አካበቢዎች በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መካነ ሰላም ከተማ ለሚገኙ የዕለት ምግብ ለሌላቸው እና በከተማው ውስጥ በከፋ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የምግብ ዱቄት ዲጋፍ በማድረግ የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል ፡፡ የመካነ ሰላም ግቢ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር አቶ አብዱሮህማን አወል ድ ጋፉን ባደረጉበት ወቅት እንደ ተናገሩት አሁን ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሚልሱትና የሚቀምሱት ያጡ ተፈናቃይ ወገኖችን ለመታደግ እና በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ በማድረግ ግቢው ካለው የውስጥ ግብአት ግምቱ 55 ሽህ ብር በላይ የሚሆን ነጭ ዱቄትና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የሆኑት አቶ መላኩ አያሌው ግብአቱን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት በአምስቱም የከተማ ቀበሌ ለሚገኙ የእለት ምግብ ለሌላችው የህብረተሰብ ክፍሎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን አመስግነው ዩኒቨርሲቲው ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ሆኖ በርካታ ስራዎችን እያገዘ ያለ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡አክለውም የማህበረሰብ አገልግሎት ፍላጎት ሰፊ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል፡፡የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ፍትፍት ጌቶ ዱቄቱን በሚያሰራጩበት ወቅት ዩኒቨርሲቲው ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸው በመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ተሰደው የመጡ በመጠለያ ጣቢያዎችና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ያሉ ከ10ሽህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ ጠቅሰው እስካሁን ድረስ የተለያዩ ረጅ ድርጅቶች፣NGO ዎችና መንግስታዊ አካላት የሚደርጉት እርዳታ የተቆራረጠ በመሆኑ በተለይ በዚህ ወቅት ለሴቶች፣ ለነፍሰ ጡር እናቶችና ለህጻናት ይህ ድጋፍ ሲደረግ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የምግብ እጥረታቸውን ይቀርፋል ብለዋል፡፡አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ለሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ መለገሱን አውስተው ይህን በጎ ተግባር መከተል እንዳለባቸው ለለጋሽ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ለሆኑና መንግስታዊ ላልሆኑ አካላት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.